ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 149:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ።

2. እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ።

3. ስሙን በሽብሰባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት።

4. እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።

5. ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።

6. የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣ባለ ሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤

7. በዚህ ሕዝቦችን ይበቀላሉ፤ሰዎችንም ይቀጣሉ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 149