ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 148:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤በላይ በአርያም አመስግኑት።

2. መላእክቱ ሁሉ አመስግኑት፤ሰራዊቱ ሁሉ አመስግኑት፤

3. ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት።

4. ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት።

5. እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።

6. ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።

7. የባሕር ውስጥ ግዙፍ ፍጥረትና ጥልቅ ውሆች ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት።

8. እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣

9. ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፣የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ፣

10. የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበሩ ወፎችም፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 148