ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 147:9-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ለእንስሳት ምግባቸውን፣የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።

10. እርሱ በፈረስ ኀይል አይደሰትም፤በሯጭም ብርታት ላይ ደስታውን አያደርግም።

11. ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፣በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።

12. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግዚአብሔርን አመስግኚ፤ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽን አወድሺ፤

13. እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፤ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአል።

14. በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል።

15. ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።

16. ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል።

17. የበረዶውን ድንጋይ ቍልቍል ይወረውረዋል፤በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን ሊቆም ይችላል?

18. ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈሳል።

19. ቃሉን ለያዕቆብ፣ሥርዐቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይገልጣል።

20. ይህን ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ አላደረገም፤እነርሱም ፍርዱን አላወቁም።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 147