ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 147:7-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።

8. ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።

9. ለእንስሳት ምግባቸውን፣የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።

10. እርሱ በፈረስ ኀይል አይደሰትም፤በሯጭም ብርታት ላይ ደስታውን አያደርግም።

11. ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፣በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።

12. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግዚአብሔርን አመስግኚ፤ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽን አወድሺ፤

13. እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፤ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአል።

14. በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል።

15. ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።

16. ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 147