ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 147:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።

16. ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል።

17. የበረዶውን ድንጋይ ቍልቍል ይወረውረዋል፤በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን ሊቆም ይችላል?

18. ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈሳል።

19. ቃሉን ለያዕቆብ፣ሥርዐቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይገልጣል።

20. ይህን ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ አላደረገም፤እነርሱም ፍርዱን አላወቁም።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 147