ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 145:6-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ስለ ድንቅ ሥራህ ብርታት ይነጋገራሉ፤እኔም ስለ ታላቅነትህ ዐውጃለሁ።

7. የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።

8. እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው፤ለቍጣ የዘገየ፣ ምሕረቱ የበዛ።

9. እግዚአብሔር ለሁሉ ቸር ነው፤ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው።

10. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግንሃል፤ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።

11. ስለ መንግሥትህ ክብር ይናገራሉ፤ስለ ኀይልህም ይነጋገራሉ፤

12. በዚህም ብርቱ ሥራህን፣የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቃሉ።

13. መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፤ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል። እግዚአብሔር ቃሉን ሁሉ ይጠብቃል፤በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

14. እግዚአብሔር የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል፤የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል።

15. የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።

16. አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።

17. እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

18. እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።

19. ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።

20. እግዚአብሔር የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ክፉዎችን ሁሉ ግን ያጠፋል።

21. አፌ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል፤ፍጡር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ቅዱስ ስሙን ይባርክ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 145