ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 145:15-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።

16. አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።

17. እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

18. እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።

19. ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።

20. እግዚአብሔር የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ክፉዎችን ሁሉ ግን ያጠፋል።

21. አፌ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል፤ፍጡር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ቅዱስ ስሙን ይባርክ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 145