ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 145:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፤ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል። እግዚአብሔር ቃሉን ሁሉ ይጠብቃል፤በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

14. እግዚአብሔር የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል፤የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል።

15. የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።

16. አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።

17. እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 145