ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 145:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።

2. በየቀኑ እባርክሃለሁ፤ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ።

3. እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤ታላቅነቱም አይመረመርም።

4. ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤ብርቱ ሥራህን ያውጃል።

5. ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤ስለ ድንቅ ሥራህም ያወራሉ።

6. ስለ ድንቅ ሥራህ ብርታት ይነጋገራሉ፤እኔም ስለ ታላቅነትህ ዐውጃለሁ።

7. የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።

8. እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው፤ለቍጣ የዘገየ፣ ምሕረቱ የበዛ።

9. እግዚአብሔር ለሁሉ ቸር ነው፤ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 145