ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 144:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እጆቼን ለጦርነት፣ ጣቶቼን ለውጊያ የሚያሠለጥን፣ እግዚአብሔር ዐለቴ ይባረክ።

2. እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤ምሽጌና ታዳጊዬ፣የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤ሕዝቤን የሚያስገዛልኝም እርሱ ነው።

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው?

4. ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያትህን ሰንጥቀህ ውረድ፤ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስስ።

6. የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤ፍላጻህን ሰደህ ግራ አጋባቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 144