ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 142:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ልመና አቀርባለሁ።

2. ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ።

3. መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፤ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል።

4. ወደ ቀኜ ተመልከት፤ እይም፤ስለ እኔ የሚገደው የለም፤ማምለጫም የለኝም፤ስለ ነፍሴም ደንታ ያለው የለም።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።

6. እጅግ ተስፋ ቈርጫለሁና፣ጩኸቴን ስማ፤ከዐቅም በላይ ሆነውብኛልና፣ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።

7. ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 142