ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 140:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ከዐመፀኞችም ሰዎች ጠብቀኝ፤

2. እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገር ያውጠነጥናሉ፤በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ።

3. ምላሳቸውን እንደ እባብ ያሾላሉ፤ከከንፈራቸውም በታች የእፉኝት መርዝ አለ። ሴላ

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፤እግሮቼንም ለመጥለፍ ከሚያደቡ ዐመፀኞች ሰውረኝ።

5. ትዕቢተኞች ወጥመድ በስውር አስቀመጡብኝ፤የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ፤በመንገዴም ላይ አሽክላ አኖሩ። ሴላ

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 140