ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 139:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ መረመርኸኝ፤ደግሞም ዐወቅኸኝ።

2. አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ።

3. መሄድ መተኛቴን አጥርተህ ታውቃለህ፤መንገዶቼንም ሁሉ ተረድተሃቸዋል።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ ገና ቃል ከአንደበቴ ሳይወጣ፣እነሆ፤ አንተ ሁሉንም ታውቃለህ።

5. አንተ ከኋላም ከፊትም ዙሪያዬን ከለልኸኝ፤እጅህንም በላዬ አደረግህ።

6. እንዲህ ያለው ዕውቀት ለኔ ድንቅ ነው፤ልደርስበትም የማልችል ከፍ ያለ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 139