ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 138:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤በአማልክት ፊት በመዝሙር እወድስሃለሁ።

2. ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ስምህንና ቃልህን፣ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

3. በጠራሁህ ቀን መልስ ሰጠኸኝ፤ነፍሴን በማደፋፈርም ብርቱ አደረግኸኝ።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፍህን ቃል በሰሙ ጊዜ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉያመስግኑህ።

5. የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና፣ስለ እግዚአብሔር መንገድ ይዘምሩ።

6. እግዚአብሔር በከፍታ ስፍራ ቢሆንም፣ ዝቅ ያለውን ይመለከተዋል፤ትዕቢተኛውን ከሩቅ ያውቀዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 138