ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 137:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።

2. እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣በገናዎቻችንን ሰቀልን።

3. የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።

4. የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!

5. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 137