ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 135:9-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ግብፅ ሆይ፤ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣በመካከልሽ ታምራትንና ድንቅን ሰደደ።

10. ብዙ ሕዝቦችን መታ፤ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።

11. የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፣የባሳንን ንጉሥ ዐግን፣የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፤

12. ምድራቸውንም ርስት አድርጎ፣ለሕዝቡ ርስት እንዲሆን ለእስራኤል ሰጠ።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህ ዘላለማዊ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

14. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፣ለአገልጋዮቹም ይራራላቸዋል።

15. የአሕዛብ ጣዖታት ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣የሰው እጅ ያበጃቸው ናቸው።

16. አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ዐይን አላቸው፤ አያዩም፤

17. ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤በአፋቸውም እስትንፋስ የለም።

18. እነዚህን የሚያበጁ፣የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።

19. የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤የአሮን ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤

20. የሌዊ ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።

21. በኢየሩሳሌም የሚኖር እግዚአብሔር፣ ከጽዮን ይባረክ።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 135