ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 135:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም ወድሱ፤እናንት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤

2. በእግዚአብሔር ቤት፣በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት።

3. እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤መልካም ነውና፣ ለስሙ ዘምሩ፤

4. እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፣እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጦአልና።

5. እግዚአብሔር ታላቅ እንደሆነ፣ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።

6. በሰማይና በምድር፣በባሕርና በጥልቅ ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ደስ ያሰኘውን ሁሉ ያደርጋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 135