ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 132:8-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ፤አንተና የኀይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ሂዱ።

9. ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”

10. ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል፣የቀባኸውን ሰው አትተወው።

11. እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤“ከገዛ ራስህ ፍሬ፣በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።

12. ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣ለዘላለም ይቀመጣሉ።

13. እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፣ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወዶአልና እንዲህ አለ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 132