ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 131:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ሐሳቤ ለዐጒል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም።

2. ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሰኘኋት፤ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።

3. እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 131