ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 13:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ?ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ድረስ ነው?

2. ከሐሳቤ ጋር የምሟገተው፣ልቤም ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው?ጠላቴስ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ድረስ ነው?

3. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ስማኝም፤የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤

4. በዚህም ጠላቴ፣ “አሸነፍሁት” እንዳይል፣ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ።

5. እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።

6. ቸርነቱ በዝቶልኛልና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 13