ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 129:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤል እንዲህ ይበል፦“ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤

2. በርግጥ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ዳሩ ግን ድል አላደረጉኝም።

3. ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ትልማቸውንም አስረዘሙት።”

4. እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው፤የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለው።

5. ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

6. ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤

7. ደግሞም ለዐጫጅ እጁን፣ለነዶ ሰብሳቢ ዕቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።

8. መንገድ ዐላፊዎችም፣“የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 129