ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 127:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።

2. የዕለት ጒርስ ለማግኘት በመጣር፣ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤እርሱ ለሚወዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።

3. እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።

4. በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።

5. ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ፣የተባረከ ሰው ነው፤ከጠላቶቻቸው ጋር በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 127