ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 120:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ከአታላይ ምላስም አድነኝ።

3. ሐሰተኛ አንደበት ሆይ፤ ምን ይከፈልህ?ከዚህስ የባሰ ምን ይደረግብህ?

4. በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል።

5. በሜሼክ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ!

6. ሰላምን በሚጠሉ መካከል፣ነፍሴ እጅግ ብዙ ጊዜ ኖረች።

7. እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፤እነርሱ ግን በተናገርሁ ጊዜ ጠብ ይሻሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 120