ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 12:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ!ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም።

2. እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ፤

3. ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣ነገር የምታበዛውንም ምላስ እግዚአብሔር ያጥፋ!

4. እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤ከንፈራችን የእኛ ነው፤ ጌታችንስ ማነው?”የሚሉ ናቸው።

5. እግዚአብሔር፣ “ስለ ድኾች መከራ፣ስለ ችግረኞችም ጩኸት፣አሁን እነሣለሁ፤በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል።

6. የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 12