ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:83-89 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

83. ጢስ የጠጣ የወይን አቍማዳ ብመስልም፣ሥርዐትህን አልረሳሁም።

84. የባሪያህ ዕድሜ ስንት ቢሆን ነው?ታዲያ፣ በሚያሳድዱኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ይሆን?

85. በሕግህ መሠረት የማይሄዱ፣እብሪተኞች ማጥመጃ ጒድጓድ ቈፈሩልኝ።

86. ትእዛዛትህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው፤ሰዎች ያለ ምክንያት አሳደውኛልና ርዳኝ።

87. ከምድር ላይ ሊያስወግዱኝ ጥቂት ቀራቸው፤እኔ ግን ትእዛዛትህን አልተውሁም።

88. እንደ ምሕረትህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ፤እኔም የአፍህን ምስክርነት እጠብቃለሁ።

89. እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃልህ በሰማይ፣ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119