ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:76-82 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

76. ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል መሠረት፣ምሕረትህ ለመጽናናት ትሁነኝ።

77. ሕግህ ደስታዬ ነውና፣በሕይወት እኖር ዘንድ ቸርነትህ ትምጣልኝ።

78. እብሪተኞች ያለ ምክንያት በደል አድርሰውብኛልና ይፈሩ፤እኔ ግን ትእዛዛትህን አሰላስላለሁ።

79. አንተን የሚፈሩህ፣ምስክርነትህንም የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ።

80. እኔ እንዳላፍር፤ ልቤ በሥርዐትህ ፍጹም ይሁን።

81. ነፍሴ ማዳንህን እጅግ ናፈቀች፤ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ።

82. “መቼ ታጽናናኛለህ?” እያልሁ፣ዐይኖቼ ቃልህን በመጠባበቅ ደከሙ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119