ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:56-64 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

56. ሥርዐትህን እከተላለሁ፤ይህችም ተግባሬ ሆነች።

57. እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ቃልህን ለመታዘዝ ቈርጫለሁ።

58. በፍጹም ልቤ ፊትህን ፈለግሁ፤እንደ ቃልህ ቸርነትህን አሳየኝ።

59. መንገዴን ቃኘሁ፤አካሄዴንም ወደ ምስክርህ አቀናሁ።

60. ትእዛዝህን ለመጠበቅ፣ቸኰልሁ፤ አልዘገየሁምም።

61. የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ፤ እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም።

62. ስለ ጻድቅ ሥርዐትህ፣በእኩለ ሌሊት ላመሰግንህ እነሣለሁ።

63. እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፣ሥርዐትህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።

64. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምድር በምሕረትህ ተሞላች፤ሥርዐትህን አስተምረኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119