ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:160-164 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

160. ቃልህ በሙሉ እውነት ነው፤ጻድቅ የሆነው ሕግህም ዘላለማዊ ነው።

161. ገዦች ያለ ምክንያት አሳደዱኝ፤ልቤ ግን ከቃልህ የተነሣ እጅግ ፈራ።

162. ትልቅ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፤በቃልህ ደስ አለኝ።

163. ሐሰትን እጠላለሁ፤ እጸየፋለሁ፤ሕግህን ግን ወደድሁ።

164. ጻድቅ ስለ ሆነው ሕግህ፤በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119