ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:155-161 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

155. ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው።

156. እግዚአብሔር ሆይ፤ ርኅራኄህ ታላቅ ነው፤እንደ ሕግህ ሕያው አድርገኝ።

157. የሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ ብዙዎች ናቸው፤እኔ ግን ከምስክርህ ዘወር አላልሁም።

158. ቃልህን አይጠብቁምና፣ከዳተኞችን አይቼ አርቃቸዋለሁ።

159. መመሪያህን እንዴት እንደምወድ ተመልከት፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ።

160. ቃልህ በሙሉ እውነት ነው፤ጻድቅ የሆነው ሕግህም ዘላለማዊ ነው።

161. ገዦች ያለ ምክንያት አሳደዱኝ፤ልቤ ግን ከቃልህ የተነሣ እጅግ ፈራ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119