ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:148-153 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

148. ቃልህን አሰላስል ዘንድ፣ዐይኔ ሌሊቱን ሙሉ ሳይከደን ያድራል።

149. እንደ ቸርነትህ መጠን ድምፄን ስማ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ሕግህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ።

150. ደባ የሚያውጠነጥኑ ወደ እኔ ቀርበዋል፤ከሕግህ ግን የራቁ ናቸው።

151. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ቅርብ ነህ፤ትእዛዛትህም ሁሉ እውነት ናቸው።

152. ለዘላለም እንደ መሠረትሃቸው፣ከጥንት ምስክርነትህ ተረድቻለሁ።

153. ሕግህን አልረሳሁምና፣ ሥቃዬን ተመልከት፤ ታደገኝም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119