ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 119:14-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ሰው በሀብቱ ብዛት ደስ እንደሚለው፣ምስክርነትህን በመከተል ደስ ይለኛል።

15. ድንጋጌህን አሰላስላለሁ፤ልቤን በመንገድህ ላይ ጥያለሁ።

16. በሥርዐትህ ደስ ይለኛል፤ቃልህንም አልዘነጋም።

17. ሕያው እንድሆን፣ ቃልህንም እንድጠብቅ፣ለአገልጋይህ መልካም አድርግ።

18. ከሕግህ ድንቅ ነገርን እንዳይ፣ዐይኖቼን ክፈት።

19. እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝ፤ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።

20. ዘወትር ደንብህን በመናፈቅ፣ነፍሴ እጅግ ዛለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 119