ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 116:6-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔር ገሮችን ይጠብቃል፤እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።

7. ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና፤

8. አንተ ነፍሴን ከሞት፣ዐይኔን ከእንባ፣እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።

9. እኔም በሕያዋን ምድር፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።

10. “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣እምነቴን ጠብቄአለሁ።

11. ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።

12. ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 116