ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 116:4-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እኔም የእግዚአብሔርን ስም ጠራሁ፤“እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ።

5. እግዚአብሔር ቸርና ጻድቅ ነው፤አምላካችን መሓሪ ነው።

6. እግዚአብሔር ገሮችን ይጠብቃል፤እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።

7. ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና፤

8. አንተ ነፍሴን ከሞት፣ዐይኔን ከእንባ፣እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።

9. እኔም በሕያዋን ምድር፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።

10. “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣እምነቴን ጠብቄአለሁ።

11. ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።

12. ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?

13. የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

14. በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።

15. የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።

16. እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፣ከእስራቴም ፈታኸኝ።

17. ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

18. በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 116