ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 116:12-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?

13. የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

14. በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።

15. የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።

16. እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፣ከእስራቴም ፈታኸኝ።

17. ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

18. በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤

19. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 116