ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 116:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት።

2. ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና፣በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።

3. የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤የሲኦልም ጣር አገኘኝ፤ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ።

4. እኔም የእግዚአብሔርን ስም ጠራሁ፤“እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ።

5. እግዚአብሔር ቸርና ጻድቅ ነው፤አምላካችን መሓሪ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 116