ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 115:2-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. አሕዛብ፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?

3. አምላካችንስ በሰማይ ነው፤እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።

4. የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ የሠራቸው፣ብርና ወርቅ ናቸው።

5. አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ዐይን አላቸው፤ አያዩም፣

6. ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤አፍንጫ አላቸው፤ አያሸቱም፤

7. እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤በጒሮሮአቸውም ድምፅ አይፈጥሩም።

8. እነዚህን የሚያበጁ፣የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።

9. የእስራኤል ቤት ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

10. የአሮን ቤት ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

11. እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

12. እግዚአብሔር ያስበናል፤ ይባርከናልም፤እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤የአሮንንም ቤት ይባርካል።

13. እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሁሉ፣ትልቁንም ትንሹንም ይባርካል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 115