ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 115:11-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

12. እግዚአብሔር ያስበናል፤ ይባርከናልም፤እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤የአሮንንም ቤት ይባርካል።

13. እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሁሉ፣ትልቁንም ትንሹንም ይባርካል።

14. እግዚአብሔር እናንተንና ልጆቻችሁን፣በባርኮቱ ያብዛችሁ።

15. ሰማይንና ምድርን በፈጠረ፣ በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ሁኑ።

16. ሰማየ ሰማያት የእግዚአብሔር ናቸው፤ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።

17. እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑት የሞቱት አይደሉም፤ወደ ዝምታው ዓለም የሚወርዱም አይደሉም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 115