ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 114:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።

4. ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ።

5. አንቺ ባሕር፤ የሸሸሽው አንቺም ዮርዳኖስ ያፈገፈግሽው ለምንድን ነው?

6. እናንተ ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ለምን ዘለላችሁ?

7. ምድር ሆይ፤ በጌታ ፊት፣በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፤

8. እርሱ ዐለቱን ወደ ኩሬ፤ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 114