ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 113:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤ የእግዚአብሔርን ስም አወድሱ።

2. ከአሁን እስከ ዘላለም፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።

3. ከፀሓይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።

4. እግዚአብሔር ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።

5. እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር፣በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?

6. በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?

7. ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤

8. ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤ከሕዝቡም ሹማምት ጋር ያስቀምጠዋል።

9. መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 113