ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 113:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤ የእግዚአብሔርን ስም አወድሱ።

2. ከአሁን እስከ ዘላለም፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።

3. ከፀሓይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።

4. እግዚአብሔር ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።

5. እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር፣በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?

6. በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 113