ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 112:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።

5. ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል፤

6. ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል።

7. ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።

8. ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።

9. በልግስና ለድኾች ሰጠ፤ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 112