ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 111:5-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።

6. ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣የአሠራሩን ብርታት አሳይቶአል።

7. የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው፤ሥርዐቱም ሁሉ የታመነ ነው፤

8. ከዘላለም እስከ ለዘላለም የጸና ነው፤በእውነትና በቅንነትም የተሠራ ነው።

9. ለሕዝቡ መዳንን ሰደደ፤ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው።

10. እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 111