ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 111:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ።በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።

2. የእግዚአሔር ሥራ ታላቅ ናት፤ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።

3. ሥራው ባለ ክብርና ባለ ግርማ ነው፤ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

4. ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤ እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው።

5. ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።

6. ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣የአሠራሩን ብርታት አሳይቶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 111