ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 11:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው።ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።

5. እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጥኡን ይመረምራል፤ዐመፃን የሚወዱትን ግን፣ነፍሱ ትጠላቸዋለች።

6. እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።

7. እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤የጽድቅ ሥራም ይወዳል፤ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 11