ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 11:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ”ለምን ትሏታላችሁ?

2. ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ?“ክፉዎች፣ እነሆ፣ ቀስታቸውን ገትረዋል፤የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።

3. መሠረቱ ከተናደ፣ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል?”

4. እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው።ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።

5. እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጥኡን ይመረምራል፤ዐመፃን የሚወዱትን ግን፣ነፍሱ ትጠላቸዋለች።

6. እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።

7. እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤የጽድቅ ሥራም ይወዳል፤ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 11