ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 108:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።

6. ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣በቀኝ እጅህ ታደግ፤ መልስልኝም።

7. እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ አለ፤ደስ እያለኝ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤“የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።

8. ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ይሁዳም በትረ መንግሥቴ።

9. ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እፎክራለሁ።”

10. ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?ወደ ኤዶምያስስ ማን ያደርሰኛል?

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?አምላክ ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋር አልወጣ አልህ!

12. አሁንም የሰው ማዳን ከንቱ ነውና፣በጠላታችን ላይ ድልን አቀዳጀን።

13. እግዚአብሔር ሲረዳን ብርቱ እንሆናለን፤ጠላቶቻችንንም ከእግሩ በታች የሚረግጥ እርሱ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 108