ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 108:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ትደርሳለች።

5. አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።

6. ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣በቀኝ እጅህ ታደግ፤ መልስልኝም።

7. እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ አለ፤ደስ እያለኝ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤“የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።

8. ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ይሁዳም በትረ መንግሥቴ።

9. ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እፎክራለሁ።”

10. ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?ወደ ኤዶምያስስ ማን ያደርሰኛል?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 108