ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 108:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤እዘምራለሁ፤ በፍጹም ነፍሴም እዘምራለሁ።

2. በገናም መሰንቆም ተነሡ፤እኔም ማልጄ እነሣለሁ።

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤በሕዝቦችም መካከል እዘምርልሃለሁ።

4. ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ትደርሳለች።

5. አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።

6. ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣በቀኝ እጅህ ታደግ፤ መልስልኝም።

7. እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ አለ፤ደስ እያለኝ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤“የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።

8. ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ይሁዳም በትረ መንግሥቴ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 108