ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 107:26-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ወደ ሰማይ ወጡ፤ ወደ ጥልቅም ወረዱ፤ከመከራቸውም የተነሣ ሐሞታቸው ፈሰሰ።

27. እንደ ሰከረ ሰው ዞሮባቸው ወዲያ ወዲህ ተንገዳገዱ፤መላው ጠፍቶባቸው የሚያደርጉትን አጡ።

28. በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

29. ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ፤የባሕሩም ሞገድ ረጭ አለ።

30. ጸጥ በማለቱም ደስ አላቸው፤ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው።

31. እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

32. በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤በሽማግሌዎችም ሸንጎ ይወድሱት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 107