ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 106:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. አባቶቻችን በግብፅ ሳሉ፣ታምራትህን አላስተዋሉም፤የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ።

8. እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ስለ ስሙ አዳናቸው።

9. ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው።

10. ከባለጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ከጠላትም እጅ ታደጋቸው።

11. ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ከእነርሱም አንድ አልተረፈም።

12. ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤በዝማሬም አመሰገኑት።

13. ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 106